የትርጉም አገልግሎቶች
ትራንስናሽናል በዓለም ውስጥ ለሚገኙ በርካታ ታዋቂ ምርቶች እና ስራ-ነክ ጉዳዮች ለአንዳንዶቹ በ24 ቋንቋዎች የትርጉም አገልግሎችን ያቀርባል። በመንግስት ደረጃ ተቀባይነት ያላቸው የጥራት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ቴክኒካዊ መስኮች ውስጥ የሚሰሩ በሙያው የሰለጠኑና የሙያ ብቃት ማረጋግጫ ያላቸው ከ1,000 በላይ የሚሆኑ ተርጓሚዎች እና 600 አስተርጓሚዎች አሉን። በዋናነት፣ በማስታወቂያ ስራዎች፣ በብሮሸሮች፣ በትምህርት፣ በቱሪዝም፣ በሕክምና፣ በሕግ እና በመንግስት ፖሊሲ ዙሪያ ያሉ ልዩ ሙያዊ ስራዎች ላይ እናተኩራለን።
ኦፊሴላዊ ሰነዶች
ኦፊሴላዊ የመንጃ ፈቃድ ሰነዶች፣ የፖሊስ ማስረጃዎች፣ የትምህርት ደረጃ ወይም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰነዶች እና ህጋዊ ሰነዶች በመስኩ በሰለጠኑ ባለሙያዎች የሚተረጎሙና ተመርምረው የሚረጋገጡ ናቸው። ተርጓሚዎቻችን፣ NZQAን NZTAን፣ WINZን፣ MPIን፣ ኢሚግሬሽንን፣ ፖሊስን፣ ጉምሩክን፣ ፍርድ ቤቶችን፣ ማረሚያ ቤቶችን፣ እንዲሁም ሌሎችንም ጨምሮ በሁሉም የኒው ዚላንድ መንግስታዊ መዋቅሮች ውስጥ ተቀባይነት ያላቸው ናቸው።
ማስተርጎም
በሙያው የሰለጠኑ አስተርጓሚዎቻችን በተለያዩ በርካታ መስኮች በ24 ቋንቋዎች ልምዱ ያላቸው ናቸው። አስተርጓሚዎች የግብብነት ክፍተትን እንደድልድይ ሆነው ለማሸጋገር የሰለጠኑ ሲሆን፣ በሙያዊ ስንምግባር ደምብ ስር ሆነው ነው ስራቸውን የሚያከናውኑት። የፖሊስ እና የፍርድ ቤት ማስተርጎምን፣ የህክምና እና የህግ መማከርን፣ ለስራ ቦታ የሚቀርብ የሙያ ስልጠናን፣ ቃለመጠይቆችን እና በሀገር-አቀፍ ደረጃ የሚካሄዱ የዓለም አቀፍ ጉባዔዎች ስራዎችን ጨምሮ፣ በሁሉም ተፈላጊ መስኮች ላይ እንረዳዎታለን። በተጨማሪም ገመድ አልባ የስብሰባ መሣሪያ እና ለመከራየት እና ለመግጠም ዝግጅ የሆነ የISO-ደረጃ ያለው የማስተርጎሚያ ድምጽ ማመቻቻ ዳስ (ቡዝ) አለን።
ዲዛይን / መረብ / ማተም
ዲዛይነሮቻችን ሁለት የውጭ ቋንቋ ተናጋሪዎች ናቸው። የርስዎ የሆነው ዓይነት ነገር፣ ምርትም ሆነ ሌላ፣ የታዳሚዎችዎን/ደንበኞችዎን ቀልብ እንዲስብ ለማድረግ፣ ምስሉ የት፣ እንዴት እና በምን መልኩ ቢቀመጥ የቱን ያክል ውጤታማ እንደሚሆን ጠንቅቀው ያውቃሉ። ብሮቸርዎ ወይም ድረ-ገጽዎ እርስዎ በሚፈልጉት መንገድ እንዲሰራልዎ ማድረግ የሚያስችለን የውጭ ቋንቋዎች ስፍትዌር ከነልምድና ዕውቀቱ አጣምረን አለን። እንደዚሁም፣ በጅምላ ሽያጭ ደረጃ የምናቀርበው ሁሉ-አቀፍ የህትመት አገልግሎትም አለን።
የፕሮጀክት ቡድን
ልክ እንደርስዎ፣ ቡድናችን “ዕውን ሰዎች” ናቸው፤ ማለትም የሙያው ልምድና ብቃት ያላቸው አስተርጓሚዎች፣ ተርጓሚዎች እና ዲዛይነሮች። እያንዳንዱን ፕሮጀክት እንደ አንድ የተለየ ስራ አድርገን ነው የምንመለከተው። ለዚህም ነው ከፍተኛ ጥራት ያለው፣ በጣም በጥብቅ ሁኒታ ተመርምሮ፣ ተፈትሾ እና ተረጋግጦ የሚወጣ፣ የርስዎን የምንጊዜም ፍላጎት የሚያረካ ሙያዊ ውጤት የምናቀርብልዎ። ኦንላይን ከኛ ጋር አብረው መስራት ይችላሉ፣ አለዚያም በኦክልናድ፣ ሀሚልተን፣ ቶውራንጋ፣ ሮቶሩዋ፣ ኒው ፕሊምዝ፣ ዌሊንግተን፣ ክራይስትቸርች ከሚገኙ ቅርንጫፎቻችን ጎራ ብለው ይጎኙን።
በነጻው ስልካችን፡ 0800 000 339 ይደውሉልንኦፊሴላዊ የመንጃ ፈቃድ ትርጉም ስራ ከ24 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች እንሰራለን።
enquiries@transnational-ltd.co.nz